የ22 ዓመቱ ስፔናዊ ከዚህ ውድድር በኋላ ጡረታ የሚወጣውን የ38 ዓመቱን ጣልያናዊ ለመርታት እስከ አምስተኛ ዙር ድረስ ለመጓዝ ተገዷል።
የተመልካችን ስሜት ሰቅዞ ይዞ 4፡30 ያህል የፈጀው ጨዋታው 7-5 6-7 7-5 2-6 እና 6-1 ተጠናቋል። አልካራዝ ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት፣ “ለፎኚኒ ይህ ውድድር ለምን የመጨረሻው እንደሆነ አልገባኝም ያለው አቅም ለተጨማሪ ሶስት እና አራት ዓመታት እንዲጫዎት ያስችለዋል” ብሏል።
የፈረንጆች 2025 ከገባ አንድም ድል ያልቀናው የ38 ዓመቱ ጣልያናዊ በበኩሉ፣ ከዓለም ቁጥር 2ቱ አልካራዝ ጋር እስከ አምስተኛ ዙር ድረስ እጫወታለሁ ብሎ እንዳልገመተ ተናግሯል። ወጣቱ ካርሎስ አልካራዝ ከ3 ሳምንታት በፊት የተካሄደውን የፍሬንች ኦፕን ክብር ጨምሮ ገና በ22 ዓመቱ አምስት የግራንድ ስላም ክብሮችን አሳክቷል።
በምሽቱ በ19 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞውን አስቆጥሏል። ተጋጣሚው የዓለም ቁጥር 138ቱ ፎኚኒ በዊምቢልደን ውድድር ከ3ኛ ዙር የተሻገረበት ታሪክ የለውም።
በ-ይበልጣል ሰውነት












