:::::::::::::::::::::::::
የመርሲሳይዱ ክለብ የእንግሊዝ የተጫዋቾች ሪከርድን አሻሽሎ የባየር ሊቨርኩሰኑን ፍሎሪያን ቪትዝ በ130 ሚሊዮን ፓውንድ አጠቃላይ ወጪ የግሉ አድርጎታል።
ተጫዋቹ በሊቨርፑል ከተማ ተገኝቶ የህክምና ሂዳቱን ማጠናቀቁ የተዘገበ ሲሆን እስከ 2030 በቀዮቹ ቤት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።
የአርን ስሎት ቡድን ከወር በፊት ከባየር ሊቨርኩሰን በተመሳሳይ ቀኝ መስመር ተከላካዩን ጀረሚ ፍሪምፖንግን ማስፈረሙ ይታወሳል።
ሊቨርፑል በግራ መስመር ተከላካይነት የበርንመዙን ሚሎስ ኬርኬዝን ዝውውርንም በዛሬው ዕለት ማጠናቀቅ ችለዋል።
የ21 አመቱን ተከላካይ በ40 ሚሊዮን ፓውንድ ያስፈረሙ ሲሆን፣የረጅም አመት ውል እንደተሰጠው ተዘግቧል።
የወቅቱ የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሊቨርፑል ቡድኑን በቀጣይ አመት ይበልጥ ለማጠናከር ከዚህ በኋላም ተጨማሪ ኮከብ ተጫዋቾችን ሊያስፈርም ይችላል ተብሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












