።።።።።።።።።።።።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ማምሻውን ፋታህ-1 ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ወደ እስራኤል ማስወንጨፉ ተገልጿል።
ተባብሶ በቀጠለው የኢራንና እስራኤል ግጭት ኢራን ምሽቱን 25 ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤን ማስወንጨፏ እየተነገረ ነው።
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኔይ በ ኤክስ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ‘ጦርነቱ ተጀመረ’ ሲሉ ጽፈዋል።
ስድስተኛ ቀኑን በያዘው የሀገራቱ ግጭትም ኢራን ፋታህ 1 ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅ
ም ላይ ማዋሏን የኢራን የሀገረ ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ። እስራኤል በበኩሏ ኢራን አስወነጨፍኩት ስላለችው ተምዘግዛጊ ሚሳኤል እስካሁን ያለችው ነገር የለም።
ኢራን እ.ኤ.አ ጥቅምት 1 2024 በእስራኤል በፈጸመችው ጥቃት በርካታ ፋታህ-1 ሚሳኤሎችን ወደ ቴልአቪቭ ማስወንጨፋ ይታወሳል።
ኢራን ፋታህ 1 ሚሳኤልን ለመጀመሪያ ጊዜ በ2023 ያስተዋወቀች ሲሆን በኢራን የበላይ መሪ አሊ ካሜኒ ስያሜውን አግኝቷል። ይህ አደጋኛ ተምዘግዛጊ ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል በሰአት 6100 ኪሎሜትር እንደሚምዘገዘግ ይነገርለታል።
ከ3000 በላይ ሚሳኤሎች እንዳሏት የሚነገርላት ቴሄራን የባለስቲክ ፣ የሀይፐርሶኒክ እና ክሩዝ ሚሳኤሎች ባለቤት ናት።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ












