፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ልክ በዚች ቀን እ.ኤ.አ ሰኔ 17 1950 በዓለም የመጀመሪያ የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተካሄደ።
የኩላሊት ንቅለ ተከላው በአሜሪካ በዶክተር ሪቻርድ ላውለር በሚመራ የህክምና ቡድን የተካሄደ ነበር።
ንቅለ ተከላውም የ44 ዓመት እድሜ ለነበራት ሩት ታከር ለተባለች ሴት ነበር። ንቅለ ተከላው አደገኛ የነበር ቢሆንም ለታከር በሕይወት ለመትረፍ ብቸኛው አማራጭ ነበር። ንቅለ ተከላውም በተሣካ መልኩ ተጠናቆ ነበር።
ታከር እ.ኤ.አ በ1955 ከኩላሊት ንቅለ ተከላ ጋር ግንኙነት በሌለው የደም ቧንቧ በሽታ የሞተች ሲሆን፤ ዶ/ር ሪቻርድ ላውለር የኩላሊት ንቅለ ተከላን ካስጀመሩ በኋላ ሌላ ንቅለ ተከላ ሰርተው አያውቅም ነበር።
የኩላሊት ንቀለ ተከላ ምርምር 1894 በኦስትሪያ በእንስሳት ላይ ተጀምሮ የተለያዩ ውጣ ውረዶችን አልፎ ከረጅም ዓመታት በኋላ የተሳካ የተባለው ንቅለ ተከላ በዚህ ቀን ተካሂዷል። ይህ የተሳካ ህክምና በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ህመምተኞች መልካም ዜና ነበር።
በ-ሔርሜላ ተመስገን












