።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራናውያን ቴህራንን ለቀው እንዲወጡ አሳሰቡ።
እስራኤልና ኢራን ለአምስተኛ ተከታታይ ቀን እርስ በእርስ እየተፋለሙ ሲሆን እስራኤል በኢራን ዋና ከተማ ጨምሮ በሌሎች ከተሞች እየወሰደችው ባለችው ጥቃት ነው ትራምፕ ኢራናውያን ቴህራንን ለቀው እንዲወጡ ያሳሰቡት።
ሁሉም ሰው ቴህራንን በአስቸኳይ ለቆ መውጣት አለበት ሲሉም በትሩዝ ማህበራዊ ሚድያ የተናገሩት ።
ተካሮ በቀጠለው የእስራኤልና ኢራን ግጭት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በካናዳ እየተካሄደ ካለው የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባዔ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ ዋሽንግተን እንደሚመለሱ ተገልጿል ።
ከትራምፕ በተጨማሪ በዚህ ሳምንት በ G7 ኮንፈረንስ አልበርታ ካናዳ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጉዟቸውን እንደሚያሳጥሩት ፎክስ ኒውስ ዘግቧል ።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ












