የ22 አመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ሊያም ዴላፕ ከሳምንታት በፊት ከኢፕስዊች ታውን ቼልሲን በ30 ሚሊዮን ፓውንድ መቀላቀሉ ይታወሳል።
ዛሬ ምሽት ከአለም የክለቦች ዋንጫ በፊት ለመገናኛ ብዙሃን አስተያየታቸውን የሰጡት የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ‘’ ዴላፕ የወደፊቱ የእንግሊዝ ቁጥር አንድ ተጫዋች ነው” ሲሉ አሞካሽተውታል።
“ተጫዋቹ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ወሳኝ አጥቂ ይሆናል” ያሉት ማሬስካ “ይህንን ስናገር በእርግጠኝነት ስሜት ነው ብለዋል። አክለውም ዴላፕ በአጥቂ መስመር ከሴኔጋላዊው ኒኮላ ጃክሰን ፉክክር እንደሚጠብቀው አንስተዋል።
ሊያም ዴላፕ ምሽት ሎስ አንጀለስን በሚገጥመው የቼልሲ የቡድን ስብስብ ውስጥ የተካተተ ሲሆን፣ በቋሚ አሰላለፍ ጨዋታውን እንደሚጀምር አሰልጣኙ ተናግረዋል።
የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ ከውሰት በተመለሱ እና በአዳዲስ ተጫዋቾች ራሱን እያጠናከረ ይገኛል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












