:::::::::::::::::::::::::::::::::::
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በምክክር ሂደቱ ዙሪያ ከምሁራን ግብዓት የማሰባሰብ እና ተቀራርቦ መስራት የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የሚመክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ምሁራኑ ለምክክር ውጤታማነት ትልቅ ሚና ስላላቸው መድረኩም እዚሁ ላይ የሚመክር ነው ብለዋል።
የሰላም እጦት ባለበት ሁኔታ ምሁራኑ ዝምታ አስፈላጊ ባለመሆኑ ሁኔታዎች ላይ ሀሳቦች እንዲሰጡ ይጠበቃል ያሉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ የምክክር ሂደት ላይ ምሁራኑ ሀሳቡን ማቅረብ ይገበዋል ብለዋል።
በሂደቱ በመሳተፍ ውጤታማነቱ ላይ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል።
ሀገራዊ ምክክር ፍጹም ነው ብለን አናስብም ስለዚህ ምሁራን ወደ መድረኩ በመምጣት ሀሳቦቻቸውን ማንሳትና መሳተፍ እንደሚገባ ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት።
ኮሚሽኑ እስካሁን የሰበሰባቸውን አጀንዳዎች የመቅረጽና የማደራጀት ስራ ላይ ስለሚገኝ ምሁራኑ ይበልጥ ወደ ሂደቱ መቅረብ እንደሚገባው ነው በመድረኩ የተጠቆመው።
ከምሁራን ጋር በሚምክረው መድረክ የሀገራዊ ምክክር ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገሥላሴ፣ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም፣ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ፣ ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው፣ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ እና ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ እንዲሁም ምሁራኖች ተገኝተውበታል።መድረኩ የምክክሩ ቀጣይ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚረዱ ሀሳቦች የሚነሱበት ነው።
በ-ሰላም ይልማ












