በአርሲ የተወለደው ቀነኒሳ በሀገር አቋራጭ፣ በጎዳና እና በሜዳ ላይ ያከናወናቸው ውድድሮች እና አንፀባራቂ ድሎቹ በታሪክ ከታዩት ታላላቅ አትሌቶች መካከል እንዲመደብ አድርገውታል።

በዓለም አቀፍ መድረከሰ ላይ ውድድር የጀመረው እ.አ.አ በ2001 ሲሆን፣ በመጀመሪያ ሩጫውም የወጣቶች ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮን የወርቅ ሜዳሊያ በማሸነፍ አጠናቅቋል። በተመሳሳይ ዓመት 3 ሺህ ሜትር ክብረ-ወሰን የሰበረ ሲሆን፣ ይህ ክብረ-ወሰን ለሦስት ዓመት ተኩል ቆይቷል።
ሀገር አቋራጭ እና የወጣቶች ሻምፒዮናን ጨምሮ ሀገራችንን ወክሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተወዳደረባቸው ርቀቶች 26 የወርቅ፣ 3 የብር እና 2 የነሐስ አጠቃላይ 31 ሜዳሊያዎችን ለኢትዮጵያ አስገኝቷል። አትሌት ቀነኒሳ በአትሌቲክሱ መድረክ የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክተሬት ተሰጥቶታል።
እኛም ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ስሟን ላስጠራው ልጇ መልካም ልደትን ተመኘን።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












