::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በሀዋሳ ቅርንጫፍ የመስክ ምልከታ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ምልከታውም የፓስፖርት አሰጣጥ፣ የእድሳት አገልግሎት፣ የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ለመከታተል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በክዋኔ ኦዲት ተቋሙ እንዲያስተካክል የተሰጡ ሥራዎች ተግባራዊነት እና የተደረጉ ለውጦችን ለመመልከት መሆኑም ተጠቁሟል።
ቅርንጫፉ ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ ሲዳማ ክልልንና ከሌሎች አጎራባች ክልሎች የሚመጡ ከ250 እስከ 370 የሚደርሱ የአዳዲስ ፓስፖርት ፈላጊዎችን በየቀኑ በመመዝገብ ላይ ይገኛል ተብሏል።
አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግም የተቋሙን አጠቃላይ ሪፎርም ተከትሎ አዳዲስ የሥራ ግብዓቶች የሟሟላትና ሥልጠና የመስጠት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል።
ከውጭ ወደ አገራት የሚገቡ እና ከአገር የሚወጡ እንዲሁም አዳዲስ ፓስፖርት ፈላጊዎች ህጋዊ ሰነድ የማረጋገጥ ሥራዎች ላይ ምልከታ በመደረግ ላይ ይገኛል።
ህገ ወጥ ደላሎችን ለመከላከልና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንዲሁም የደንበኞች አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶችን ጥምር ኮሚቴው በመመልከት ላይ ይገኛል።
በክዋኔ ኦዲት የተመላከቱ ምቹ የሥራ አካባቢ መፍጠር፣ ስትራቴጂዎችና ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ማድረግና ከፀጥታና ሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ ለመሥራት ያደረጋቸው ጥረቶችም የምልከታው አካል ናቸው።












