በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከባየር ሙኒክ ኮትራቱ ጨርሶ የተለያየው ሳኔ ወደ ጋላታሳራይ ለመሄድ ተስማምቷል።
የ29 አመቱ የመስመር አጥቂ ወደ ሰሜን ለንደኑ አርሰናል ይሄዳል በሚል በስፋት ሲዘገብ ቢቆይም፣አሁን ላይ ተጫዋቹ ከቱርኩ ክለብ ጋር በግል ጉዳዮች ከስምምነት መድረሱ ተዘግቧል።
ለጋላታሳራይ ቅርበት ያላቸው የቱርክ ሚዲያዎች እንደዘገቡት የክለቡ ሃላፊዎች ከተጫዋቹ ጋር በሁሉም ጉዳዮች መግባባት ላይ ናቸው ብለዋል።
የቀድሞው የማንችስተር ሲቲ ተጫዋች በአሜሪካው ሜጀር ሊግ ሶከር ቡድኖችም ሲፈለግ ቆይቷል።
ሊሮይ ሳኔ በባየር ሙኒክ በነበረው የ5 አመት ቆይታ 40 ግቦችን ሲያስቆጥር፣21 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን ለቡድን ጓደኞቹ ማድረስ ችሏል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












