አትሌት ገለቴ ቡርቃ ለአመታት ያከማቸሁት ሃብት ንብረቴ በባለቤቴ ተዘረፍኩ በሚል በመገናኛ ብዙሃን ቀርባ መናገሯ ይታወሳል።
ትላንት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቷን ጉዳይ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ከገለቴ ጎን እንደሚቆም በምሽቱ የዜና እወጃችን መዘገባችን አይዘነጋም።
ዛሬ ረፋድ በማህበራዊ ሚዲያ የአትሌት ገለቴ ባለቤት አቶ ታደለ ገብረመድህን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤን ቢሲ ኢትይዮጵያ ተናግረዋል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












