ተጫዋቹ መጠኑ ባይገለጽም በኖርዌይ ሊግ ታሪክ ሪከርድ በሆነ ክፍያ ወደ እንግሊዝ እንደሚመጣ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
አርሰናል፣ አስቶን ቪላና ጂሮናን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ስቨሪ ንይፓንን ለማስፈረም ከፍተኛ ጥረት አድርገው እንዳልተሳካላቸው ዘገባው አስረድቷል።
አርሰናል ለማግባባት ለንደን ድረስ ጋብዞ እንዳመጣው ቪላ ደግሞ ለመደራደር ኖርዌይ ድረስ እንደተጓዘ ተሰምቷል።
ሆኖም ግን አንዳቸውም ፊርማውን ሊያገኙ አልቻሉም።
ማንችስተር ሲቲ ከረፈደ ወደ ፉክክሩ ቢገባም ተጫዋቹንና ቤተሰቦቹን ማሳመን እንደቻለ የዘ አትሌቲክ ዘገባ አስረድቷል።
ወደ ማንችስተር ሲቲ ከመጣ በኋላ በቂ ልምድ እንዲያገኝ ወዲያውኑ በረዥም ጊዜ የውሰት ውል ለሌላ ክለብ ይሰጣል ተብሏል።
የ18 ዓመቱ አማካይ ስቨሪ ንይፓን ለሮሰንበርግ ዋናው ቡድን 70 ጨዋታዎችን አድርጓል።
በ2024 የውድድር ዓመት 8 ጎሎችን አስቆጥሮ ለቡድን አጋሮቹ 6 ጊዜ አመቻችቶ አቀብሏል።
የኖርዌይ ከ21 ዓመት በታች ቡድን ተጫዋቹ ስቨሪ ንይፓን ከአርሊንግ ሀላንድ፣ ማርቲን ኦዲጋርድና አንቶኒዮ ኑሳ በኋላ ተስፋ የተጣለበት ኖርዌያዊ ነው።
በ-ይበልጣል ሰውነት












