።።።።።።።።።።።።።።።
የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ስፔንን በመለያ ምት አሸንፎ የ2024/25 የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ሻምፒዮን መሆን ችሏል!
ምሽት በአሊያንዝ አሬና በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፣ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በመደበኛው 90 ደቂቃ እንዲሁም በተጨማ የ30 ደቂቃ ጨዋታ 2 ለ 2 አቻ ተጠናቀዋል።
የፖርቹጋልን ግቦች ኑኖ ሜንዴዝ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሲያስቆጥሩ፣ የስፔንን ግቦች ደግሞ ዙቢሜንዲ እና ኦያርዛባል ከመረብ አሳርፈዋል።
አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት ባመራው ጨዋታ ፖርቹጋል ስፔንን 5 ለ 3 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስታለች።
ይህ ለፖርቹጋል ሁለተኛው የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ዋንጫ ሲሆን፣ ዋንጫውን ሁለት ጊዜ ያሳካ የመጀመሪያው ብሔራዊ ቡድን ሆና ታሪክ ሰርታለች።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ደግሞ ለብሔራዊ ቡድኑ 138ኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።












