የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ፖቼቲኖ ከሰሞኑ ወደ ቀድሞ ክለባቸው ይመለሳሉ ሲባል ቆይቷል።
ቶተንሃም ሆትስፐር አሰልጣኝ አንጅ ፖስትኮግሉን የይሮፓ ሊግ ዋንጫን ካሳኩም በኋላ ማሰናበቱ ይታወሳል።
ክለቡ በፕሪምየር ሊግ 17ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን፣አመታዊውን አጠቃላይ ውጤት በመገምገም አሰልጣኙ ከሃላፊነታቸው አንስቷል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም በማፈላለግ መሆኑ ታውቋል።
ፖቼቲኖ ቶተንሃምን በፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ተፎካካሪ በማድረግ፣የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ እንዲሆን በማስቻል ክለቡን ጠንካራ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በ2019 ክለቡን ከለቀቁ ወዲህ በፒኤስጂ አሁን ደግሞ በአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን እየሰሩ ይገኛል።
የ53 አመቱ ፖቼቲኖ ወደ ቀደመ ክለባቸው ይመለሱ እንደሆን ሲጠየቁ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል።
“መላው ትኩረቴ ብሄራዊ ቡድኑ በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ስኬታማ ማድረግ ነው” ያሉት “ፖቼቲኖ ከቶተንሃም አሰልጣኝነት ጋር ስማቸው መያያዙ ሃሰተኛ መረጃ ሲሉ” አጣጥለዋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












