ልክ በዛሬዋ ቀን ሰኔ 2 ፣ 1963 ዓ.ም በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ከአሜሪካ ጋር በመስማማት የተፈረመው ፈር ቀዳጅ ስምምነት ነበር።
የዚህ ስምምነት ዋና ዓላማ በወቅቱ በኢትዮጵያ የተሰራጨውን የወባ በሽታን ለመቆጣጠር ያለመ ነበር።
በወቅቱ በኢትዮጵያ የወባ በሽታ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የችግሩ ሰለባ ሆነው ነበር።
ይህ በኢትዮጵያ የተከሠተው የወባ ወረርሽኝ የአለም አቀፉ ማህበረሰብን አነጋግሮ ነበር። በወቅቱ የነበረው የአሜሪካ መንግስትም ከፍተኛ ድጋፍ በመስጠት ይህንን ችግር ለማቃቃል ከኢትዮጵያ ጋር ተግባራዊ ስራ ተሠርቶ ነበር።
በዚህ የተነሳ የወባ በሽታን ከኢትዮጵያ ሙሉበሙሉ ለማጥፋት የተደረገው ድርሻ ታሪካዊ አስተዋፅኦ ነበረው።
በ – ሔርሜላ ተመስገን












