፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።
ሩዋንዳ ከማዕከካዊ አፍሪካ ቀጠናዊ ጥምረት ራሷን አገለለች።
ኪጋሊ በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባለው ግጭት ላይ እጇ አለበት በሚል ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት ተፈጥሮባታል፡፡
ሩዋንዳ የማዕከላዊ አፍሪካ አገራትን የኢኮኖሚ ማህብረሰብ (Eccas) የሊቀመንበርነት ቦታን ትረከባለች ቢባልም ሳይሆን ቀርቷል፡፡
በባለ 11 ዓባላቱ ህብረት የሊቀመንበርነቱን ሚና ለዓባላቱ እያፈራረቀ የሚሰጥ ቢሆንም ሩዋንዳ በዚህ ዓመት ለዚህ አልታደለችም፡፡
በኢኳቶሪያል ጊኒ በተደረገው ስብሰባ ላይ ተከልክላለች።

ሊቀመንበርነቱን መረከብ መብቴ ነው ያለችው ኪጋሊ “ሆነ ተብሎ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ፍላጎት ለማሳካት ጫና ለመፍጠር የተደረገ ነው” ስትል በምላሹ ወንጅላለች፡፡
በጥምረቱ ለመቆየት ጠቃሚ ነገር አላገኘሁም በሚል ነው ለመውጣት የወሰነችው ፡፡
በአሜሪካ አሸማጋይነት ሩዋንዳ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በዚህ ወር መገባደጃ ላይ ሊፈረም የሚችል ረቂቅ የሰላም ዕቅድ ላይ እየተነጋገሩ ባሉበት ሰዓት ነው አዲስ ውጥረት የተፈጠረው፡፡
ጥምረቱ ሩዋንዳ ጦሯን ከዴሞክራቲክ ኮንጎ እንድታስወጣ አስጠንቅቆ የኪጋሊ ሀይሎች በኪንሻሳ ላይ እንደዘመቱም እውቅና ሰቷል።
ችግሮች እስከሚፈቱ ኢኳቶሪያል ጊኒ በሩዋንዳ ምትክ የማዕከላዊ አፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ ሊቀመንበር ሆና ትቀጥላለች።
ሮይተርስ እንዳስነበበው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












