ኢንተር ሚላን ሳይጠበቅ ከአሰልጣኝ ሲሞኒ ኢንዛጊ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ተተኪ የሚሆኑ ብቁ አሰልጣኞችን በማፈላለግ ላይ ይገኛል።
በኮሞ ለሁለት የውድድር አመት ድንቅ ቡድን መስራት የቻለው ፋብሪጋስ፣ የኢንዛጊ ተተኪ እንዲሆን በኢንተር ባለስልጣናት በኩል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ተነግሯል።
ዘ ሰን የጣሊያን መገናኛ ብዙሃንን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው የኢንተር ሰዎች የኮሞን ሃላፊዎች በዚሁ ጉዳይ ላይ ማነጋገራቸው ታውቋል።
የ38 አመቱ ወጣት አሰልጣኝ ፋብሪጋስ ከሳምንታት በፊት በጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን የአሰልጥነን ጥያቄ ቀርቦለት ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
ፋብሪጋስ ኮሞን ከሴሪ ቢ ወደ ሴሪ ኤ ባሳደገበት አመት 10ኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ አድርጎታል።
ስፔናዊው የኮሞ አሰልጣኝ ብቻ ሳይሆን በክለቡ የባለቤትነት ድርሻ ስላለው ለኢንተር ሚላን ፋብሪጋዝን ማግኘት ያስቸግረዋል ተብሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












