::::::::::::::::::::::
ድሪው ቢኒስኪ በመባል ይታወቃል በአለም ከሚገኙ ሀገራት 197 ጎብኝቷል። በአሪዞና ተወልዶ ያደገው ቢኒስኪ የጉዞ ታሪኩ የጀመረው የኮሌጅ ትምህርቱን ለመማር በሄደባት አውሮፓ ነው።
ቢኒስኪ እንደገለፀው እ.ኤ.አ በ2012 ለትምህርት ወደ አውሮፓ በመሔዱ ያያቸው የተለያዩ ባህሎች ቀልቡን መሳብ እንደጀመሩት ይገለጻል።
በቀጣይ መዳረሻውን ያደረገው ለስራ ወደሄደባት ደቡብ ኮርያ ነው። በደቡብ ኮርያ ያገኛቸው ልምዶችም በጉዞዎቹ ላይ እንዲጠናከር አደረጉት።
ባለፋት ጥቂት አመታት ውስጥ አደገኛ ናቸው ተብለው የሚታሰብ ሀገራትን የመጎብኘት እድል የገጠመው ቢኒስኪ አሁንም ይሔን ልምድ ማጠናከር እንደሚፈልግ ይገልጻል።
በጉዞውም አፍጋኒስታን፣ ቬንዙዌላ፣ ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ፓኪስታን፣ ሊቢያ እና ኢራንን መመልከት ችሏል። ስለ ሠዎች እና ባህል አዎንታዊ ታሪኮችን በማካፈል ያልተዛባ አመለካከትን መፍጠር እንደሚፈልግ የሚገልጸው ቢኒስኪ ተጓዥ ለመሆን ለሚመኙ ልጆች አርአያ መሆን ዋና አላማ እንደሆነም ይናገራል።
በ – ሔርሜላ ተመስገን












