June 3, 2025
የ’ኢትዮጵያ ታምርት’ ንቅናቄ እንደ አማራ ክልል በጎንደር ከተማ የማጠቃለያ መርሀግብር እየተደረገ ነው። በክብር እንግድነት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ የተገነባውን ከአኩሪ አተር ግብዓት በከፊል የተቀነባበረ ዘይት የሚያመርት ቲቲኬ የዘይት ፋብሪካን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ላይ፣ ፋብሪካው እንደሀገር ለጀመርነው የአምራች የኢንዱስትሪ ልማት ሁነኛ አብነት ነው ብለዋል። በ373 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፋብሪካው፤ በቀን 120 ቶን የአኩሪ አተር ዱቄት እና በከፊል የተጣራ ዘይት የማምረት አቅም አለው ተብሏል።
በ-ሃብተማርያም መንግስቴ












