የስፔኑ ሃያል ክለብ ባርሴሎና ባለፉት 5 አመታት ከፍይናስ ኪሳራ እና ዕዳ በተገናኝ ስሙ እየተያያዘ ሲዘገብ መስማት እየተለመደ ሆኗል።
ብሉግራናዎቹ በሜዳ ላይ በዋንጫ የታጀበ ውጤታማነት ላይ ቢሆኑም፣ በስፔን በዚሁ የፍይናንስ ቀውስ መነሻነት ከላሊጋው አወዳዳሪ አካል ጋር በሚገባበት ሰጥ አገባ ወደ ፍርድ ቤት በማቅናት ጭምር ሙግት ሲገጥም ታይቷል።
ባርሴሎናን የተመለከተ ሰፊ ዘገባ ይዞ የወጣው ቢቢሲ ስፖርት፣ በተለይም የስፖርቲንግ ዳይሬክተሩን ዴኮ አንደበት ጠቅሶ የክለቡን ፋይናስ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ቆይታ አድርጓል።
በተጠናቀቀው የስፔን የእግር ኳስ ውድድሮች ባርሴሎና በሃገር ውስጥ የሶስዮሽ ዋንጫ ባለድል በመሆን ነግሷል። በተመሳሳይ ጊዜ የክረምት የዝውውር ገበያ ሲከፈት የፋይናንስ ኪሳራውን ለመሸፈን እና ሂሳቡን ለማስተከከል ቁልፍ ተጫዋቾቹን ይሸጣል የሚል መረጃ፣በተለይም በስፔን ሚዲያዎች በስፋት ሲዘገብ ቆይቷል።
ብራዚላዊው ዴኮ ክለቡን በተመለከተ የሚሰራጩ ዘገባዎች የተሳሳቱ ናቸው ያሉ ሲሆን፣ባርሴሎና ተጫዋቾቹን የሚለቅበት ምንም ምክንያት የለውም፣እንደሚዘገበው የተጋነነ የፋይናንስ ቀውስ አላጋጠመንም ሲሉ ተናግረዋል። ለዚህም በማሳያነት የሚያቀርቡት ለቁልፍ የቡድኑ አባላት በቅርቡ የተደረገውን የውል ማሻሻያ ነው።
የካታላኑ ክለብ ከሳምንታት በፊት ዋና አሰልጣኙን ሃንሲ ፍሊክ፣የባለንዶር እጩውን ራፊኒሃን እና ብርቅዬውን ኮከባቸው ላሚን ያማልን ለተጨማሪ አመታት በክለቡ የሚያቆያቸውን ውል አስፈርሟል።
ዴኮ አስተያየታቸውን በመቀጠል በአውሮፓውያኑ 2023 መጀመሪያ ክለቡን በስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሃላፊነት ሲረከቡ የፋይናንስ ውስንነት እንደነበር አንስተው፣ይህ ግን ሊፈጠር የቻለው በስፔን ካለው የፋይናንስ ደንብ ህግጋቶች መጥበቅ ጋር ተያይዞ መሆኑን አንስተዋል። ዴኮ በእንግሊዝ ያለው የፋይናንስ ደንብ እኛጋ ባለው ልክ አይጠብቅም የላሊጋ አወዳዳሪውን ተቋም ወቅሰዋል።
“ይህ የፋይናንስ ተመሳሳይ ችግር በሁሉም የስፔን ክለቦች የሚታይ ነው” ያሉ ሲሆን ትልክ ክለብ ስለሆንን ወሬ ይገንብናል ብለዋል። ከላሊጋው አወዳዳሪ ተቋም ጋር ስላላቸው ግንኙነትም ተጠይቀው በመግባባት እየሰሩ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ዴኮ ይህንን ይበሉ እንጂ ባርሴሎና የአማካኝ ስፍራ ተጫዋቹን ዳኒ ኦልሞን በላሊጋው የቡድን ስብስብ ለማስመዝገብ የገጠመውን ችግርና ከላሊጋው አወዳዳሪ ባለስልጣናት ጋር የገባበት ውዝግብ አይዘነጋም።
የክለቡን የፋይናንስ አቅም በተመለከተ አልተዳከመም በሚል ደጋግመው የሚያነሱት ዴኮ፣ ከናይኪ ጋር ባርሴሎና ስለፈጸመው ታሪካዊ ስምምነት እና 100ሺ ታዳሚዎችን እንዲያስተናግድ ተደርጎ እየታደሰ ስለሚገኝው ኑ ካምፕም ተናግረዋል።
ከፊታቸው ባለው የዝውውር ገበያም ቡድኑን ይበልጥ ለማጠናከር ሶስት ያህል ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርሙ አስታውቀዋል።
ለክለቡ ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች እና ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት ግን ክለቡ በተለይም የሮበርት ሌቫንዶቭስኪ ተተኪ የሚሆን አጥቂ ማስፈረሙ የማይቀር ነው ያሉ ሲሆን፣የተጋነነ ክፍያ ወጪ የማድረግ ፍላጎት ግን የለውም ብለዋል።
የማንችስተር ዩናይትዱ ማርከስ ራሽፎርድ ላይ ፍላጎት ቢያሳዩም፣ዩናይትድ የሚጠይቀውን 40 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል አይችሉም ተብሏል።
ዴኮ ለማስተባበል ቢፈልጉም ክለቡ ከፍተኛ ዕዳ የተጫነው በመሆኑ ፣ አዳዲስ ተጫዋቾችን ቢያመጣም በአነስተኛ ገንዘብ እና በነጻ ሂሳብ ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
👇👇👇👇👇👇
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV












