ከሠሞኑም ቻይና R1 የተሰኘውን ሞዴል ማሻሻሏን አስታውቃለች፡፡ አዲሱ ሞዴል R1-0528 የሚል ስያሜን አግኝቷል።
R1 በበርካታ ቋንቋዎች ተጠቃሚዎችን የሚያገለግል ሲሆን በሂሳብ፣ በኮዲንግ እና በምክንያታዊ አስተሳሰብ (reasoning) ዘርፎች የላቀ አፈጻጸም አለው፡፡
የኩባንያው እርምጃ ከOpenAI እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋር ያለውን ፉክክር ይበልጥ እንዳጠናከው ተነግሯል።
የኩባንያው ውጤት ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳበ ሲሆን፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የቻይናን ተወዳዳሪነት በቀዳሚነት ያስቀጥላል ሲሉ ብዙዎች ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ነው፡፡
የኩባንያው አመራሮች አዲሱ ሞዴል የመረጃ ትንተና፣ የጽሑፍ ፈጠራ፣ የፕሮግራም ኮድ መጻፍ፣ የሂሳብ ስሌት መስራት እና ሌሎች ውስብስብ ተግባራትን በከፍተኛ ፍጥነት እና ትክክለኛነት ማከናወን እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
ዲፕሲክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያስመዘገበ የሚገኘው ውጤት የቻይናን የቴክኖሎጂ አቅም የሚያሳይ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የ”ኤአይ” ፈጠራዎችን ማፍራት እንደምትችል አመላካች ነው፡፡
ባሳለፍነው ወር DeepSeek ኩባንያ ይፋ ባደረገው መረጃ በአማካይ 97 ሚሊዮን ወርሃዊ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ገልጿል፡፡
በ-ሃሴት ሀይሉ












