June 2, 2025
የኢትዮጵያ የእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የዑለማ ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ ሼክ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በሳዑዲ ዓረቢያ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሀጅ ኮንፈረንስ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ሼኽ ኢብራሂም ጅዳ ኪንግ አብዱልአዚዝ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በጅዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጄነራል አምባሳደር ጣፋ ቱሉ፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮሚዩኒቲ ተወካዮችና የሀይማኖት አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
የሀጅ ስነ-ስርዓት ከመካሄዱ በፊት ለአንድ ቀን በሚካሄደው በዚህ ኮንፍረንስ ላይ ለስነ-ስርዓቱ ስለተደረገው ዝግጅት እና በምን መልኩ መሄድ እንዳለበት የሚመከርበት መሆኑን የጄዳ ጽ/ቤት ረዳት ኃላፊ መሀመድ አወል ለኢቢሲ ዶትስትሪም ተናግረዋል፡፡ በየዓመቱ በሚካሄደው በዚህ ኮንፍረንስ የየሀገራቱ የእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮች የሚሳተፉበት መሆኑንም ኃላፊው አያይዘው ጠቁመዋል፡፡
በበሳዑዲ ቆይታቸው ከዓለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ለሚገነባዉ የነጃሺ መስጂድ እና ኢስላማዊ የምርምር ማዕከል ግንባታ በተመለከተ እንደሚወያዩ ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ገልፀዋል፡፡













