ሊቨርፑል 20ኛ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ድሉን ለማክበር 15 ኪሎ ሜትር ርቀት በሸፈነ የጎዳና ክብረ በዓል ማድረጉ ይታወሳል።
በሺዎች የሚቆጠሩ የቀዮቹ ደጋፊዎች አደባባይ በወጡበት ሰዓት ፖል ዶይል የተባለ የ53 አመት ጎልማሳ መኪናውን እያሽከረከረ በደጋፊዎች ላይ አደጋ አድርሷል።
በአደጋው ህይወቱን ያጣ ደጋፊ ባይኖርም ቁጥራቸው 79 የሚደርሱ ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ማስተናገዳቸውን ፖሊስ ማስታወቁ ይታወሳል።
የቀድሞ የባሕር ሃይል አባሉ ዶይል በምን ምክንያት መነሻ ይህንን አደጋ እንዳደረሰ ግልጽ ባይሆንም፣ ዛሬ ጠዋት ፍርድ ቤት ቀርቧል።
ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ከተላኩ ሰዎች መካከል የ9 አመት ታዳጊን ጨምሮ ጽኑ አካላዊ ጉዳት የገጠማቸው 7 ደጋፊዎች እስካሁንም በህክምና ላይ ይገኛሉ።
ወንጀለኛውን በ7 ዋና ዋና ጥፋቶች የከሰሰው የሊቨርፑል ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ወንጀል በሚል ክሱን አክብዶበታል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












