የኢፕስዊች ታውኑን የፊት መስመር አጥቂ በርካታ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቡድኖች የራሳቸው ለማድረግ እየተንቀሳቃሱ ሲሆን፣ተጫዋቹ ፍላጎቱ ወደ ቼልሲ መጓዝ መሆኑን ገልጿል።
ዘ አትሌቲክ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የተጫዋቹ ክለብ ባለፉት ቀናት የተላያዩ ቡድኖችን ጥያቄ ሲያስተናግድ ሰንብቷል።
በአጥቂ መስመር ላይ ተጫዋች በማፈላለግ ላይ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች ኢፕስዊችን አነጋግረው ተጫዋቹ ወደ ምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ መሄድ ብቸኛው ፍላጎቱ መሆኑን ገልጸውላቸዋል።
ሌላኛው የእንግሊዛዊው አጥቂ ፈላጊ ኒውካስል ዩናይትድ እና ሌሎች አምስት ክለቦችም የተጫዋቹ የመጨረሻ ውሳኔ ተነግሯቸዋል።
የ22 አመቱ ዴላፕ በቀጣይ ቼልሲን ለመቀላቀል በግል ጉዳዮች እና የውል ማፍረሻ ክፍያ ዙሪያ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ሊያም ዴላፕ ከእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በመጣ በአመቱ በተሰናበተው ኢፕስዊች በውድድር አመቱ 12 ግቦችን ከመረብ አገናኝቷል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












