፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ኤም ፖክስ በሽታ በዝንጀሮ በጂነስ ኦርቶፖክስ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በአካል ንክኪ ወይም በበሽታው ከተያዙ እንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፍ እና በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችል በሽታ ነው፡፡
የኤም ፖክስ ቫይረስ በዴንማርክ (1958) በዝንጀሮዎች ውስጥ የተገኘ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ልጅ ላይ የተገኘው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ነው፡፡ በቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተያዘው የዘጠኝ ወር ህጻን ነበር፡፡
እ.ኤ.አ. በ1980 የፈንጣጣ በሽታን ማጥፋት እና የፈንጣጣ ክትባት በአለም አቀፍ ደረጃ ማብቃቱን ተከትሎ፣ ኤም ፖክስ በመካከለኛው ምስራቅና ምዕራብ አፍሪካ ያለማቋረጥ ብቅ እያለ ይገኛል።
እ.ኤ.አ. በ2003 በአሜሪካ የተከሰተው ወረርሽኝ ከውጭ ከሚገቡ የዱር እንስሳት ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ ከ2005 ጀምሮ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የተጠረጠሩ ህሙማን ተገኝተዋል።
እ.ኤ.አ. በ2022 በ Clade I MPXV ምክንያት የኤም ፖክስ ወረርሽኝ በሱዳን ሪፐብሊክ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ ተከስቷል፡፡
የመተላለፊያ መንገዶች
ቫይረሡ ካለባቸው ሠዎች እንዲሁም እንስሣቶች ጋር ባለ ንክኪዎች፣ በእንስሳት ንክሻ፣ በቫይረሱ የተያያዘ ሰው የተጠቀመበትን እቃ መጠቀም፣ ከህመምተኛው ላይ ከሚወጡ ቁስለቶች ጋር የሚደረግ ንክኪ ናቸው።
የበሽታው ምልክቶች
ሽፍታ፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ የእጢ እብጠት፣ የቆዳ ቁስለትና ድካም፣ የጡንቻና የጀርባ ህመም የበሽታው ምልክቶች ናቸው።
መከላከያ መንገዶች
ከላይ የተገለፁት ምልክቶች ባሉባቸው ታማሚዎች አካባቢ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን በመጠቀም፥
የኤም ፖክስ መሰል ሽፍታ የሚታይባቸው ሰዎች ጋር ባለመነካካትና ታማሚዎቹ የተጠቀሙባቸውን ቁሳቁሶች፣ አልባሳትና መኝታ በአግባቡ ሳያጸዱ ባለመጠቀም፣ የግልና የእጅ ንፅህና በመጠበቅና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል ይቻላል።
በሽታው በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች የሚያሳይ ማንኛዉም ሰዉ በሚገኝበት ጊዜ፣ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም መሄድ ይገባል።
ምንጭ St. Paul’s Hospital Millennium Medical College
በ-ሔርሜላ ተመስገን












