::::::::::::::::::::::::::
የጣሊያን ሴሪኤ ሻምፒዮን ክለብ የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር አጥቂ ላይ ካሳለፍነው የውድድር አመት አንስቶ ፍላጎት ማሳየቱ ይታወሳል።
ማንችስተር ዩናይትድ በይሮፓ ሊግ ፍጻሜ ከተሸነፈ በኋላ አሰልጣኙ ለታዳጊው ተጫዋች ክለብ እንዲፈልግ መንገሩን ዘ አትሌቲክ ዘግቦታል።
የ20 አመቱ ጋርናቾ በውድድር አመቱ እጅግ ደካማ አቋም አሳይተዋል በሚል ለሽያጭ ከቀረቡ ተጫዋቾች ቀዳሚው ነውም ተብሏል።
የኔፕልሱ ክለብ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ጂኦቫኒ ማና የተጫዋቹን የዝውውር ጉዳይ በተመለከተ ለመወያየት ወደ እንግሊዝ ማቅናታቸው ታውቋል።
ናፖሊ ባሳለፍነው የውድድር አመት አማካኙን ስኮት ማክቶሚናይን ከማንችስተር ዩናይትድ ወስደው ተጫዋቹ አስደናቂ የውድድር አመት በማሳለፍ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ሽልማት አግኝቷል።
አሌሃንድሮ ጋርናቾ በያዝነው የውድድር አመት በሁሉም የውድድር መስኮች 11 ግቦችን ሲያስቆጥር፣10 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ዩናይትድ ከአርጀንቲናዊው ታዳጊ ዝውውር 40 ሚሊዮን ፓውንድ ይፈልጋል ተብሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












