::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ሁለት የእስራኤል ኤምባሲ ዓባላት በዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ ተገደሉ፡፡
የኤምባሲ ሰራተኞቹ በአይሁድ ሚውዚየም አቅራቢያ አሊያም ከሚውዚየሙ ውጭ ነው የተተኮሰባቸው፡፡
ፖሊስ የሰላሳ ዓመት ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን እንዲህ ዓይነቱን የሽብር ድርጊት አንታገስም ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡
የሜትሮፖሊታንቱ ፖሊስ ዲፓርትመንት ሀላፊዋ
ፓሜላ ኤ ስሚዝ የ30 ዓመቱ የቺካጎው ኢሊያስ ሮዲርጌዝ ከጥቃቱ ጋር በተገናኘ በቁጥጥር ስር መዋሉን ይፋ አድርገዋል።
ተኩስ ከመክፈቱ በፊት ተጠርጣሪው ከሚውዚየሙ ውጭ ሲንቀሳቀስ ነበርም ብለዋል።
ወደ አራት ሰዎች ተጠርጣሪው ከተጠጋ በኋላ ተኩስ ከፍቶ ሁለቱን የእስራኤል ኤምባሲ ዓባላት ህይወት ቀጥፏል፡፡
ስሚዝ እንደሚሉት ተጠርጣሪው ሮድሪጉዌዝ“ነጻ!ነጻ ፍልስጤም !” የሚል መፈክር ሲያዝ አሰምቷል፡፡
ፖሊስ የተጠርጣሪው የጥቃት ፍላጎት ምንድን ነው የሚለውን በማጣራት ላይ መሆኑንም አስገንዝቧል፡፡
የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ አስተዳደራቸው ይህን ዓይነት የሽብር ድርጊት ቆሞ እንደማይመለከተው እና እንደማይታገሰውም አስጠንቅቀዋል፡፡
በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ ሟቾቹ ለጋብቻ እየተዘጋጁ የነበሩ ጥንዶች ናቸውም ብሏል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም ቢሆኑ በዋሽንግተን የተፈጸመው ጥቃት ምንጩ ጸረ-ሴማዊነት ነው ብለውታል፡፡
ዘገባው የሲ ኤን ኤን እና ኤን ቢ ሲ ኒውስ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












