ውሃ ሰማያዊዎቹ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት በሜዳቸው ከቦርንመዝ በሚያደርጉት ጨዋታ ለአስር አመት በአማካኝ መስመር ያገለገላቸውን ኬቭን ደብሯይነን ይሸኛሉ።
ለቤልጂየማዊው ሁነኛ ተተኪ ይሆንልናል በማለት በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ግፊት ማንችስተር ሲቲ የባየር ሊቨርኩሰኑ አማካኝ ፍሎሪያን ቪትዝን ለማስፈረም ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።
በርካታ ፈላጊዎች ያሉት ቪትዝ ወደ እንግሊዝ መጓዝ ምርጫው ቢሆንም፣ባርሴሎና እና ፒኤስዤም ፍላጎታቸውን አሳይተዋል።
በተጫዋቾች የዝውውር ጉዳይ ታማኝነት ያላቸውን መረጃዎች በማቅረብ የሚታወቁ የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት፣ አሁን ላይ ማንችስተር ሲቲ ከተጫዋቹ ዝውውር ሙሉ በሙሉ ራሱን አግልሏል።
ክለቡ ከቅርብ አመታት ወዲህ ዝውውርን በተመለከተ በያዘው ፖሊሲ ምክንያት ከጀርመናዊው ተጫዋች ጨረታ ወጥቷል።
ማንችስተር ሲቲ ማስፈረም የሚፈልገውን ተጫዋች የመሸጫ ዋጋ በተመለከተ ይገባዋል ከሚለው ሂሳብ ውጪ፣ አቅሙ እንኳን ቢኖረውም የተጋነነ ክፍያ እንደማይፈጽም በዴክላን ራይስ ዝውውር አሳይቷል።
ባየር ሊቨርኩሰን ለ 22 አመቱ አማካኝ ፍሎሪያን ቪትዝ 140 ሚሊዮን ዩሮ የጠየቀ ሲሆን ከዚህ በታች በሆነ ሂሳብ ተጫዋቹን መቀቅ አይፈልግም ተብሏል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












