። ። ። ። ። ። ። ። ።
በቀዳሚነት ቀን 9 ሰዓት በደረጃ ሰንጠረዥ በአንድ ነጥብ የሚበላለጡት ሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ ይገናኛሉ።
ሲዳም ቡና በጥሩ ወቅታዊ አቋም ላይ የሚገኝ ሲሆን ባለፉት 5 ጨዋታዎች ምንም አይነት ሽንፈት አልገጠመውም፣በሶስቱ ድል ማድረግ ሲችል በሁለቱ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
የጦና ንቦቹ በአንጻሩ ከደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች፣በአሸናፊነት የተወጡት በአንዱ ብቻ ነው። በሶስቱ ሽንፈት ሲገጥማቸው፣በሁለቱ ድልና የአቻ ውጤት አስመዝግበዋል።
ምሽት 12 ሰዓት ሐዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።
ለወራት በወራጅ ቀጠናው የነበረው ሐዋሳ ባለፉት ሳምታት ባሳየው ተደናቂ የውጤት መሻሻል፣ደረጃውን በማሳደግ 12 ስፍራ ላይ ተቀምጧል።
ካደረጋቸው ያለፉ አምስት ጨዋታዎች በ4ቱ ድል ማደረግ የቻለ ሲሆን ሽንፈት አልገጠማቸውም። የሰበሰቡት 34 ነጥብ አሁንም ከወራጅ ቀጠናው ያራቃቸው በ4 ነጥብ በመሆኑ በቀሪ ጨዋታዎች ነጥብ መሰብሰብ የግድ ይላቸዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ 7ኛ ደርጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ጨዋታውን በድል ከተወጣ በጊዜያዊነት ወደ 4ኛ ስፍራ የሚያድግበት ዕድል አለው።
ፈረሰኞቹ ባሳለፍነው ሳምንት ሽንፈት እስኪገጥማቸው ድረስ እንደ ሐዋሳ ሁሉ በጥሩ በነቃቃት ላይ በመገኘታቸው ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎታል።
መርሐግብሮቹ በተያዘላቸው ሰዓት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይደርጋሉ።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












