ሰሜናዊ መብራቶች(Northern Lights) ወይም አውሮራ ቦሪያሊስ በአብዛኛው በሰሜናዊው የዓለም ክፍል ማለትም በአርክቲክ ክልል አካባቢ በሰማይ ላይ የሚታዩ ውብ እና አስደናቂ የብርሃን ትርኢቶች ናቸው። ይህ የብርሃን ትርኢት እንደ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ እና ወይን ጠጅ ያሉ የተለያዩ ተለዋዋጭ ቀለሞችን ያሳያል።
እነዚህም ቀለሞች ከፀሐይ የሚመጡ በሰዓት እስከ 72 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር (45 ሚሊዮን ማይል) በሆነ ፍጥነት ከምድር የከባቢ አየር ጋዞች ጋር ሲጋጩ ይፈጠራሉ እነዚህ ተንቀሳቃሽ ቀለሞች የሚመነጩት ከፀሐይ ነበልባሎች በሚመጡ በኤሌክትሪክ ኃይል የተሞሉ ቅንጣቶች ከምድር ከባቢ አየር ጋር በመገናኘታቸው ሲሆን ይህም አስደናቂ ውጤት ይፈጥራል።
ከከተማ መብራቶች ርቀው የሚገኙ ቦታዎች ለዕይታ ምቹ ሲሆኑ እንደ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ፊንላንድ፣ አይስላንድ፣ ግሪንላንድ፣ ካናዳ እና የአሜሪካ ግዛት በሆነችው አላስካ ያሉ ቦታዎች ለመመልከት ቆንጆ ቦታዎች ናቸው። በእነዚህ ሰሜናዊ አገሮች የክረምት ቱሪዝም ይህንን የብርሃን ክስተት ለመመልከት በሚመጡ ጎብኚዎች ምክንያት ከፍተኛ ጭማሪ ያሳያል።
በ-ሀና ተሰማ












