በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚሠራጨው ኡሱቱ በመባል የሚታወቀው ቫይረስ እንደተቀሰቀሰ የእንግሊዝ እንስሳት እና ዕፀዋት ጤና ኤጀንሲ ገልጿል። እነዚህ ጥቁር ወፎች በሚፈጥሩት የተለየ ዜማ በይበልጥ ይታወቃሉ።
ኤጀንሲው እያደረገ ባለው ጥናትም ቫይረሱ በትንሽ ጊዜ ውስጥ መስፋፋት መቀጠሉን እና የወፍ ዝርያዎቹንም ቁጥር እ.አ.አ ከ 2020 ጀምሮ በ 40% ያክል ቁጥራቸው እንደቀነሰ አብራርቷል።
በአሁን ጊዜም በደቡብ፣ በምዕራብ እና በሠሜን እንግሊዝ ይሄ ቫይረስ እንደተከሰተ ተመላክቷል። ቫይረሡ ከአምስት ዓመት ወዲህ የመሠራጨት አቅሙን ጨምሯል።
ዘገባው የBBC ነው፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን












