:::::::::::::::::::::::::::::::::
ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ከተማ 84 ዓለም አቀፍ ኮንፍረሶች መካሄዳቸው ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከኤንቢሲ ኢትዮጵይ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው የሀሳብ መዋጮ መድረክ ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ከተማ 84 ዓለም አቀፍ ኮንፍረሶች መካሄዳቸው ተጠቁሟል፡፡
ከተማዋ በቀሩት ጥቂት ወራትም 20 የሚደርሱ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን ለማካሄድ በእቅድ ላይ ናት ተብሏል፡፡

የሀሳብ መዋጮ መድረኩ በዘርፉ የተሰማሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ውይይት እያካሄዱ ሲሆን አዲስ አበባ የቱሪዝም ዘርፉን በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ መሆኗም ተነስቷል፡፡
ቢዝነስ ቱሪዝምን ለማሳደግ ከተለያዩ አገራትን የሚመጡ ቱሪስቶችን ያማከለ አገልግሎትን መዘርጋት ፤ሰላማዊ አከባቢን መፍጠር እና ቴክኖሎጂ ማጎልበት ላይ አበክሮ መስራት እንደሚጠይቅ ነው በአጽንኦት የተነሳው፡፡

በአዲስ አበባ የቢዝነስ ቱሪዝምን ማስፋፋት ለሁለንተናዊ እድገት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ነው ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በ-ሰላም ይልማ












