ፀጉርዎ እየሳሳ ነው ወይስ እየረገፈ ነው? ጭንቀት ከምክንያቶቹ አንዱ ሊሆን ይችላል!
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ብዙዎቻችን ጭንቀት በአዕምሯችን እና አካላችን ላይ ስለሚያደርሰው ተጽእኖ እናውቃለን። ግን ጭንቀት የፀጉር መርገፍ ሊያስከትል እንደሚችል ያውቃሉ?
ሰውነታችን ለጭንቀት በተለያየ መንገድ ምላሽ ሲሰጥ፣ ፀጉራችን ብዙ ጊዜ የዚህ ሁኔታ ተጠቂ ይሆናል ጭንቀት ሥር በሰደደ ጊዜ፣ የፀጉር ከረጢቶች ፀጉር ማብቀል ሙሉ በሙሉ እስከማቆም ሊደርሱ ይችላሉ።
ጭንቀት በፀጉርዎ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ፡-
የፀጉር መሳሳት (Telogen Effluvium): ስሜታዊ ወይም አካላዊ ጭንቀት የፀጉር ሀረጎችን ወደ “እረፍት” እንዲገፉ ያደርጋቸዋል። ይህ ሁኔታ ቴሎጅን ኤፍሉቪየም (Telogen Effluvium) ይባላል። በመደበኛነት፣ የተወሰኑ የፀጉር ሀረጎች ብቻ በእረፍት ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን በጭንቀት ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሀረጎች ያለጊዜያቸው ወደ እረፍት ደረጃ በመግባት ከ2-3 ወራት በኋላ መርገፍ ይጀምራሉ፣ ይህም የፀጉር መሳሳትን ያስከትላል። ፀጉርዎ ከመደበኛው በላይ እየረገፈ እንደሆነ ከተሰማዎ፣ ይህ የጭንቀት ምልክት ሊሆን ይችላል።
የፀጉር መሰባበር (Hair Breakage): ጭንቀት የሰውነትን አጠቃላይ ጤና ይጎዳል። ይህም የፀጉርዎን ጥንካሬ እና የመለጠጥ አቅም በመቀነስ እንዲዳከም ያደርጋል። የተዳከመ ፀጉር በቀላሉ ይሰበራል፣ ይህም ፀጉርዎ ቀጭንና ደረቅ እንዲመስል ያደርገዋል።
እንደ አልፔሲያ አሪያታ ያሉ ሁኔታዎች መከሰት ወይም መባባስ፡- በአንዳንድ ሁኔታዎች ጭንቀት እንደ አልፔሲያ አሪያታ (Alopecia Areata) ያሉ ራስን የመከላከል ሁኔታዎችን (Autoimmune conditions) ሊያስከትል ወይም ሊያባብስ ይችላል።
በአልፔሲያ አሪያታ ወቅት፣ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት በስህተት የራሱን የፀጉር ሥር ያጠቃል። ይህ ደግሞ በጭንቅላት፣ በጺም ወይም በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ ፀጉር ሙሉ በሙሉ በሚረግፍበት ሁኔታ ይታያል። ጭንቀት የእነዚህን ሁኔታዎች ምልክጽ ሊያነሳሳ ወይም የከፋ ሊያደርጋቸው ይችላል።
ታዲያ ምን ማድረግ አለብን?
ጭንቀትን መቆጣጠር (Stress Management): ፀጉርዎ ጤናማ እንዲሆን፣ ጭንቀትን መቀነስ ወሳኝ ነው። ለራስህ ጊዜ በመስጠት ዘና ለማለት መሞክር እንደ ዮጋ፣ ማሰላሰል (meditation)፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (exercise)፣ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች (hobbies) ወይም ከጓደኞችና ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፤ ጭንቀትን የሚቀንሱ እንቅስቃሴዎችን መለማመድ በቂ እንቅልፍ ማግኘትም ለጭንቀት አያያዝ ወሳኝ ነው።
ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ (Balanced Nutrition): ለፀጉር ጤንነት አስፈላጊ የሆኑ ቪታሚኖች እና ማዕድናት የበለፀገ ምግብ መመገብ ። እንደ ፕሮቲን፣ ዚንክ፣ ባዮቲን፣ ቫይታሚን A, C, D እና E ያሉ ንጥረ ነገሮች ለፀጉር እድገትና ጥንካሬ ወሳኝ ናቸው። ትኩስ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቅባት የሌላቸው ስጋዎች፣ ጥራጥሬዎች እና ለውዝ በብዛት ይመገቡ።
ባለሙያ ያማክሩ (Consult a Professional): የፀጉር መርገፍ ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ከተሰማዎት ወይም ስጋት ካለዎት፣ በፍጥነት ሕክምና ማግኘት ተጨማሪ የፀጉር መርገፍን ስለሚከላከል ባለሙያ (የቆዳ ህክምና ባለሙያ) ያማክሩ። ባለሙያዎች የመርገፉን መንስኤ በትክክል ለይተው በማወቅ ተገቢውን ህክምና ሊመክሩ ይችላሉ።
ያስታውሱ! ፀጉርዎ የአጠቃላይ ጤናዎ ጠቋሚ በመሆኑ ትኩረት መስጠት አይርሱ
በ-ሃና ተሰማ












