።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ከሐዋሳ ከተማ፣ሲዳማ ቡና ከመቻል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
የ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ2 ጨዋታዎች ቀጥሎ ይደረጋል።
7 ሰዓት የጀመረው ድሬዳዋ ከተማን ከሐዋሳ ያገናኘው ጨዋታ ስቱዲዮ እስከገባንበት ሰዓት ድረስ ጎል አልተቆጠረበትም።
ድሬዳዋ ከወራጅ ቀጠና በ1 ነጥብ ርቀት ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ተጋጣሚው ሐዋሳም እንዲሁ ከወራጅ ስፍራ በአስተተማኝ ሁኔታ ለመራቅ ሶስት ነጥቡን ይፈልጉታል።
በሊጉ 15ኛ ላይ የተቀመጠው ሐዋሳ ከተማ ጨዋታውን ድል ማድረግ ከቻለ ደረጃውን የማሻሻል ዕድል አለው።
10 ሰዓት ሲል ሲዳማ ቡና ከ መቻል ይገናኛሉ ሁለቱም ቡድኖች በድንቅ ወቅታዊ አቋም ላይ የሚገኙ መገኘታቸው ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎታል።
39 ነጥብ በመያዝ 5ኛ ላይ የተቀመጠው መቻል ከሲዳማ የ3 ነጥብ ብልጫ አለው ጨዋታውን ድል ማድረግ ከቻለ በጊዜያዊነት ደረጃውን ወደ 4ኛ ያሳድጋል።
9ኛ ላይ የሚገኘው ሲዳማም ደረጃውን የሚያሻሽልበት ጨዋታ በመሆኑ ከፍተኛ ትንቅንቅ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












