ስሞል ፖክስ በሚባል የሚታወቀው የፈንጣጣ በሽታ ልክ በዚህች ቀን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ግንቦት 8 1980 በአለም ጤና ድርጅት አማካኝነት ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ ተገልፅ ነበር፡፡
ፈንጣጣ በቫሪዩላ ቫይረስ የሚመጣ ከባድ ተላላፊ በሽታ ነው ፈንጣጣ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከሚያሳዩት ምልክቶች መካከልም ከፍተኛ የሆነ ትኩሳትና ልዩ የሆነ የቆዳ ላይ ሽፍታን ያሳያል ብዙ ከፈንጣጣ የተረፉ ሰዎች በትላልቅ የሰውነት ክፍሎቻቸው ላይ በተለይ ደግሞ በፊታቸው ላይ ቋሚ የሆነ ጠባሳ ሰለባ ናቸው፡፡
የፈንጣጣ በሽታ ከመጥፋቱ በፊት በዋነኝነት የተሰራጨው እርስ በእርስ ንክኪዎች ነበር፡፡ በአሜሪካ የመጨረሻው የፈንጣጣ ወረርሽኝ የተከሰተው እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ 1949 ነበር፡፡ ዘገባው የCDC America ነው፡፡












