ነገር ግን ዩናይትዶች በዚህ ክረምት አምበላቸው ብሩኖን ሊሸጡ እንዳማይችሉ ተገልጿል።
እንደ ዴይሊ ስታር ዘገባ፣ አል- ሂላል ለ28 ዓመቱ ፖርቱጋላዊ አማካይ የ3 ዓመት ኮንትራት ለመስጠት ዝግጁ ነው።
የሳውዲው ሀያል ክለብ ባለስልጣናት ከፈርናንዴዝ ጠበቃ ካኤታኖ ማሪያ እና ከወኪሉ ሚጌል ሩበን ጋር ንግግር የጀመሩ ሲሆን ክለቡ የፖርቱጋላዊውን አማካይ የፋይናንስ ጥያቄ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን አሳውቀዋል።
ከተጫዋቹ ተወካዮች ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ከቻሉ አል-ሂላል ጥያቄውን ለፕሪሚየር ሊጉ ክለብ በይፋ ያቀርባል ተብሏል።
የ28 ዓመቱ ተጫዋች በኦልድትራፎርድ ያለው ኮንትራት እስከ ሰኔ 2027 ድረስ ይቆያል።
የባለፈው ዓመት የሳውዲ ፕሮ ሊግ አሸናፊው አል- ሂላል ከእሲያ ሻምፒዮንስ ሊግ በአል- አህሊ ተሸንፎ ከግማሽ ፍጻሜው ነበር የተሰናበተው።
በሳውዲ ፕሮ ሊግም በአል- ኢቲሀድ በ6 ነጥብ ልዩነት እየተመራ እንደመሆኑ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማዘዋወርና አሰልጣኝ ለመቅጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ክለቡ ከሰሞኑ አሰልጣኝ ሆርጌ ጀሱስን ካሰናበተ በኋላ ጆዜ ሞሪንሆ፣ ማርኮ ሲልቫና ኑኖ ኢስፕሪቶ ሳንቶ ላይ አይኑን መጣሉ ተነግሯል።
በ-ይበልጣል ሰውነት












