የቶተንሃም ሆትስፐሩ ተከላካይ በክረምት ክለቡን ለመልቀቅ መወሰኑን ተከትሎ ወደ ስፔን ላሊጋ ሊያቀና እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።
በአትሌቲኮ ማድሪድ እየተጫወተ የሚገኘው የአገሩ ልጅ ሁሊያን አልቫሬዝ “ሮሜሮ እንደሚቀላቀለን ተስፋ አደርጋለሁ” ሲል አስተያየት መስጠቱ ክለቡ በዝውውሩ ጉዳይ ገፍቶ መጓዙን አመላካች ነው ተብሏል።
አልቫሬዝ አስተያየቱን ሲቀጥል “በአትሌቲ የመልበሻ ክፍሉ ድባብ ብሎም ከተማዋ ማድሪድ ለአርጀንቲናውያን የተመቸች ናት’’ ሲል ለቅርብ ጓደኛው መልዕክት አስላልፏል።
በታሪኩ እጅግ ደካማ የውድድር አመት እያሳለፈ የሚገኘው ቶተንሃም፣ ምንም እንኳን በክረምት ተጫዋቾቹን ማቆየት ቢፈልግም የአውሮፓ ውድድር ተሳትፎን ካላረጋገጠ አስቸጋሪ ይሆንበታል።
በተለይ በተከላካይ መስመር ጉልህ ክፍተት እያለበት ሮሜሮን ለመልቀቅ ባይፈልግም፣ አትሌቲ ተጭኖ ከመጣ ተጫዋቹ መውጣቱ የማይቀር ይሆናል።
አትሌቲኮ ማድሪድ በክረምት የዝውውር መስኮት የ27 አመቱ ተከላካይ የመጀመሪያ ፈራሚ ሊያደርገው እንደሚችል ተዘግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












