የአርሰናሉ ተከላካይ በሎስብላንኮዎቹ በጥብቅ እየተፈለገ ሲሆን ያለፉትን ሳምንታት የተጫዋቹን ወኪሎች ማነጋገራቸው ታውቋል።
የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሌ ኪፕ እንደዘገበው ሪያል ማድሪዶች በመድፈኞቹ የሚጠየቀውን ክፍያ ፈጽመው ተከላካዩን የግላቸው ማድረግ ይፈልጋሉ።
ሳሊባ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር ሁለት አመት የሚቀረው ኮንትራት አለው።
ማድሪድ ያለፉትን አመታት እንደሚያደርገው ተጫዋቹ ኮንትራቱን ሲጨርስ በነጻ የመውሰድ ፍላጎት አለው ቢባልም፣ በተከላካይ መስመር ያለበትን ክፍተት ለመሙላት በክረምት ፈረንሳዊውን ለመውሰድ ተዘጋጅተዋል።
የአርሰናል ባለስልጣናት የ24 አመቱ ሳሊባ በክለቡ እንደሚቆይ መተማመን አላቸው ቢባልም፣ ተጫዋቹ የሪያልን ጥያቄ ሊየጤነው ይችላል ተብሏል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












