የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በ84ኛው የአርበኞች የድል ቀን ባስተላለፉት መልዕክት ሚያዝያ 27 በፋሺስት ጣሊያን ላይ ድል የተቀናጀንበት ብቻ ሳይሆን የቅኝ ግዛት እስቤ እንዲንኮታኮት ያደረግንበት ነው ብለዋል።
ከኢትዮጵያ አርበኞች የምንማረው ለአገር የሚሰጥ ፍቅር፣ቁርጠኝነትና መስዋትነት ነው ብለዋል።
እንዲሁም አርበኞች የአገር ታላቅነት በውል በመገንዘብ መስዋትነት በመክፈል አገርን ለትውልዱ ለማስተላለፍ ያላቸውን ጽኑ ፍላጎት የድል ቀኑ ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ አሁን ኢትዮጵያ እድገቷን እያፋጠነች የምትገኝበት ጊዜ ላይ መሆኗን በመጠቆም የኢትዮጵያን እድገት ለማፋጠን ሁሉም ለሰላም ጎበዝ መሆን አለበት ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል።
በ-ሰላም ይልማ












