፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ኦዴሳ ከተማ ከፍተኛ የተባለ የአየር ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተነገረ።
በጥቃቱ በርካታ መሰረተ ልማቶች የወደሙ ሲሆን ሁለት ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል አምስት ሰዎችም ቆስለዋል።
ሩሲያ ፈፅማዋለች በተባለው በዚህ የድሮን ጥቃት ትልልቅ ህንፃዎችና ትምህርት ቤቶች ስለመውደማቸውም ተነግሯል።
ከኦዴሳ ባሻገር ካርኪቭና ሱሚ በተባሉ የዩክሬን ከተሞች ፍንዳታ መሰማቱ ተገልጿል።

ሩሲያ ፈፅማዋለች በተባለው በዚህ ከፍተኛ የአየር ጥቃትን ተከትሎ እስካሁን የሰጠችው ምላሽ አለመኖሩም ተነስቷል።
“ከጠላት ሀገር የአየር ላይ ጥቃት ተፈፅሞብናል በርካታ መሰረተ ልማቶችና ንፁሀን ዜጎች ተጎድተውብናል” ሲሉ የኦዴሳ ከንቲባ ጄኔዲ ትሩካኖቭ ተናግረዋል።
ኦዴሳ በጥቁር ባህር የምትገኝ ስትራቴጂካዊ የወደብ ከተማ ስትሆን አንድ ሚሊዮን ዜጎች መኖሪያ ናት።
የአሁኑን ጨምሮ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ሩሲያ ተደጋጋሚ ጥቃት በከተማዋ ትሰነዝራለች።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












