የመብራት መቆራረጡ በመላው ስፔን እና ፖርቹጋል በአስር ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ፈታኝ የሆነ ሲሆን በከፊል ወደነበረበት መመለሱ ተገልጿል፡፡
የሀይል መቆራረጡ ቢስተካከልም ይህን ከፍተኛ የመብራት መቆራረጥ ያስከተለው ምክንያት ምን እንደሆነ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው ተብሏል፡፡ በሀይል መቆራረጡ ሳቢያ የትራንስፖርት አገልግሎቶች የተስተጓጎሉ ሲሆን፣ የህዝብ ማመላለሻ እና የአውሮፕላን ማረፊያ ስራዎችን ተቋርጠዋል፡፡
በርካታ የንግድ ድርጅቶችም ስራቸውን ያቆሙ ሲሆን የሀገራቱ መሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። የሀይል መቆራረጡ ወደ ነበረበት የተመለሰ ሲሆን አንዴ በተፈጠረው መቆራረጥ ምክኒያት የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት አሁንም ቀናት ሊወስድ እንደሚችል ተነግሯል፡፡
በፈረንሳይም ተመሳሳይ ክስተት በመከሰቱ የፈረንሳይ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያዎች ለጥቂት ደቂቃ ከስራ ውጪ ሆነው ነበር ተብሏል፡፡ በሞሮኮ ውስጥ ያሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎችም አገልግሎታቸውን ለማስቀጠል ሲታገሉ እንደነበር ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
በ-ሊያ ክብሮም












