። ። ። ። ። ። ። ። ።
በቴህራን እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የአፍሪካ-ኢራን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ኮንፈረንስ እና በ7ተኛው የኢራን ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ላይ በኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሐሰን ሞዓሊን የተመራ የልዑካን ቡድን በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
3ተኛው የአፍሪካ-ኢራን የንግድ ኮንፈረንስ እና 7ተኛው የኢራን ኤክስፖ 2025 እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 27-ሜይ 1 የሚካሄድ ነው።
እ.ኤ.አ. ከኤፕሪል 27-28 የሚካሄደው የአፍሪካ-ኢራን ኢኮኖሚ ኮንፈረንስ በዋናነት በኢራን እና በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የኢንዱስትሪ፣ የንግድና የኢቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር አተኩሮ የሚካሄድ መሆኑም ተገልጿል።
የኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዝሽኪያን በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢራን በጤና፣ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ እና በግብርና ያስመዘገበችውን ስኬት በሚመለከት ልምድ፣ ተሞክሮና ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ አገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
በኢራንና በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን በመጪው ዓመት ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ መታቀዱም በኮንፈረንሱ ላይ ተጠቁሟል።
ኮንፈረንሱ በዘይትና ጋዝ፣ ፔትሮኬሚካል፣ ፋርማሲውቲካልና ኬሚካል ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና ማዕድን ኢንዱስትሪዎች፣ እንዲሁም የግብርና እና ኤነርጂ ንግድና ኢንቨስትመንት ላይ አተኩሮ እንደሚካሔድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።












