፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
ትላንት በግማሽ ፍፃሜ ሲዳማ ቡና ከ መቻል ያደረጉት መርሃ ግብር መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ባዶ ለባዶ በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።
ሁለቱን ቡድኖች ለመለየት በተደረገ የመለያ ምት ሲዳማ ቡናዎች 7ለ6 በማሸነፍ ለፍፃሜ ማለፍ ችለዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍጻሜ የደረሰው ሲዳማ ቡና ሸገር ከተማን ጥሎ ካለፈው ከወላይታ ዲቻ ተገናኝቷል።
በወላይታ ዲቻ እና ሲዳማ ቡና መካካል የሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታው ግንቦት 30 ቀን 2017 እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የውድድሩ አሸናፊ ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ እንደሚሆን ይታወቃል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












