። ። ። ። ። ። ። ። ።
ደቡብ አፍሪካ ሉዓላዊነቷን እንደምታስጠብቅ ገዥው አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ አሳወቀ፡፡
ከአሜሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ በገባችበት ሰዓት ነው ደቡብ አፍሪካ ይህን ብርቱ ምላሽ የሰጠችው፡፡
ኤ ኤን ሲ ፓርቲ ከአዲሱ የመሬት ህግ ጋር በተገናኘ አሜሪካ የምታቀርበውን ውንጀላ ያጣጣለው ሲሆን፣ ጉዳዩን ከሉዓላዊነት አንጻር እመለከተዋለሁ ብሏል፡፡
“ነጻ እና ሉዓላዊ አገር ነን፤ የማንንም ጣልቃ ገብነት እንዲሁ አንቀበልም” ብሏል ፓርቲው፡፡
በተለይም “እኛ የአሜሪካ ግዛት አይደለንም እናም ሉዓላዊነታችን በሚገባ ይከበራል” የሚል መረጃ አጋርተዋል የኤ ኤን ሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የደቡብ አፍሪካ አዲስ የመሬት ህግ ጥቂት ቁጥር ያላቸውን የጎሳ ዓባላት ዋጋ ያስከፍላል በሚል መቃወማቸው ይታወሳል፡፡
መንግስት ያለምንም ካሳ የእነዚህን ሰዎች ሀብት እና መሬት ይወስዳል የሚል መከራከሪያ ያላቸው የአሜሪካ ፖለቲከኞች የሲሪል ራማፎሳን መንግስት ከወነጀሉ ሳምንታት ነጉደዋል፡፡
ህጉ አግላይ እና ዘረኝነት የተላበሰ አሰራርን የተከተለ ነው ባይ ናት ዋሽንግተን፡፡
ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳም አዲሱ ህግ ህዝቡን በእኩልነት እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የመሬት ሀብት ተደራሽነቱ ይረጋግጥለታል በሚል በተደጋጋሚ ሀሳባቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡
ዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












