፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
አትሌት ትዕግስት አሰፋ 45ኛውን የለንደን ማራቶን 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ጨርሳ በበላይነት አጠናቃለች።
የፓሪስ ኦሎምፒክ የብር ሜዳልያ አሸናፊዋ ትዕግስት፣ የገባችበት ሰዓት የሴቶች ብቻ ማራቶን የዓለም ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።
ኬንያዊቷ ጆይሲሊን ጄፕኮስፔ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ፣ በውድድሩ የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ተሰጥቷት የነበረችው አትሌት ሲፋን ሀሰን ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሳለች።
በተመሳሳይ በወንዶች ማራቶን በተደረገው ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ 5ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ኬንያዊው አትሌት ሴባስቲያን ሳው 2 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ27 ሴኮንድ በመግባት በአንደኝነት አጠናቋል።
በግማሽ ማራቶን የአለም ሪከርድ ባለቤት ዩጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ ሁለተኛ መውጣት ሲችል፣ ኪንያዊው ሙቲሶ ሙንያኦ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












