ለአንድ ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዪ ፕሮግራሞች የሚከበረው የመረጃና የዲጅታል ጤና ሳምንትን በይፋ ተጀምሯል።
የጤና ሚኒስቴር አራተኛው ሐገር አቀፍ የመረጃና የዲጅታል ጤና ሳምንትን “ከመረጃ ወደ ተግባር፡ ለመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ እመርታ” በሚል መሪቃል ነው እያካሄደ የሚገኘው።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በመክፈቻ መርሃግብሩ ባደረጉት ንግግር ሁሉን አቀፍ የጤና ተደራሽነት ለማሳካት የመረጃ ስርዓትን መዘርጋት የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ በሚከበረው የመረጃና የዲጅታል ጤና ሳምንት በዘርፉ የተገኘውን ስኬት ለመረዳት፣ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም እና ችግሮችን ለይቶ ለማውጣት የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ መረጃን የመሰብሰብ፣የመተንተን እና የመጠቀም አቅምን በጤናው ዘርፍ ለማጠናከር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።
አራተኛው ሐገር አቀፍ የጤና መረጃ ሳምንት ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች በተለያዪ ፕሮግራሞች ይከበራል።
በ-ሰላም ይልማ












