33ተኛ ሳምንት መርሃግብሩን ያደረገው የላሊጋው መሪ ባርሳ በተጋጣሚው ላይ ፍጹም የጨዋታ ብልጫ መውሰድ ችሏል።
ብሉግራናዎቹ 13 ኢላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ቢችሉም ወደ ግብ መለወጥ የቻሉት አንዱን ብቻ ነው። ከጉዳት የተመለሰው ዳኒ ኦልሞ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ አገናኝቷል።
አሁን ላይ ባርሴሎና ከተከታዩ ሪያል ማድሪድ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 7 በማሳደግ ተደላድሏል።
ዛሬ ምሽት ከሜዳቸው ውጪ ሄታፌን የሚገጥሙት ሎስ ብላንኮዎቹ የነጥብ ልዩነቱን የማጥበን ዕድል አላቸው።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












