ኮሚሽኑ ላከው እንዳስታወቀው ከበዓሉ አስቀድሞ በ11ዱ ክፍለ ከተሞች ለማህበረሰቡ ሰፊ የግንባቤ ማስጨበጥ ስራ ማከናወኑን ገልጿል።
የእምነት ተቋማት እና የገበያ ስፍራዎችን ጨምሮ ህዝብ በሚበዛባቸው ስፍራዎች የጥንቃቄ መልዕክቶች መተላለፋቸውን አመልክቷል።
በተከናወነው የቅድመ ጥንቃቄ ስራ በበዓሉ ዋዜማ ከአንድ ቀላል አደጋ በስተቀር በሰላም ማለፉን ጠቁሟል።
በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጉራራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በምግብ ማብሰያ ላይ ባጋጠመ አደጋ የ20 ሺህ ብር ንብረት መውደሙን ኮሚሽኑ በመረጃው አመልክቷል።
በበዓል ወቅት ከሚኖረው የአደጋ ስጋት ተጋላጭነት አኳያ ዋዜማው በሰላም እንዳለፈም ተጠቅሷል።
ህብረተሰቡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ በመተግበሩ በአከባበር ሂደቱ አደጋዎች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉም ነው የተገለጸው።
ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ በመተግበር ላሳየው ትብብርም ምስጋናውን በማቅረብ የበዓሉ ድባብ ዛሬን ጨምሮ ለቀጣይ ቀናት የሚቆይ በመሆኑ የተለመደ ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።
ማህበረሰቡ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ካጋጠመ በነጻ የስልክ መስመር 939፣ በቀጥታ 0111-55-53-00 ወይም በ0111-56-86-01 እንዲያሳውቅም ጥሪ አቅርቧል ዘገባው የኢዜአ ነው።












