:::::::::::::::::::::::::::::::
የቀዮቹ አንበል በክረምት ኮንትራቱ የሚጠናቀቅ የነበረ ሲሆን ክለቡን ሊለቅ ይችላል ሲባልም ቆይቷል።
ኔዘርላንዳዊው ተካላካይ ከመሃመድ ሳላህ ኮንትራት ማራዘም በኋላ እርሱም ውሉን ሊያድስ እንደሚችል ሲዘገብ ቆይቷል።
የመርሲሳይዱ ክለብ በማህበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው የ 33 አመቱ ተጫዋች ለቀጣይ ሁላት አመት ለመቆየት መስማማቱን አስታውቋል።
የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ የተቃረበው ሊቨርፑል፣ የወሳኝ ተጫዋቾቹን ኮንትራት ማደሱ ለክለቡ ትልቅ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ተገምቷል።
ክለቡ በክረምት ኮንትራታቸው ይጠናቀቅ ከነበሩት ቨርጅል ቫንዳይክ፣መሃመድ ሳላህ እና አርኖልድ፣ ሁለቱን በክለቡ ማቆየት ችሏል።
የ26 አመቱ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ነክረምት ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል መስማማቱ ይታወሳል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ

See insights
Boost a post
Like
Comment
Share












