የጸሎተ ሐሙስ ሥነ-ሥርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ነው
NBC Ethiopia
የጸሎተ ሐሙስ ሥነ-ሥርዓተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ነው፡፡ በሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቀሳውስትና ምዕመናን ተገኝተዋል።
የእምነቱ ተከታዮች ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ ለሓዋርያቱ ያሳየውን ትሕትና በሕይወታቸው ሊገልጡት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ ጸሎተ ሀሙስ ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ የሓዋርያቱን እግር ያጠበበት እና ትሕትናን ያስተማረበት ዕለት ነው።

ጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን
በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ልደታ ማርያም ካቴድራል ቤተክርስቲያን የሥነ ሥርዓቱ አካል የሆነው መስዋዕተ ቅዳሴ እየተካሄደ ይገኛል። በቤተክርስቲያኒቱ ጸሎተ ሐሙስ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች የሚታሰብ ሲሆን÷ ሚስጥረ ቁርባን እና ሚስጥረ ክህነትም በፀሎተ ሐሙስ የተመሰረቱ ሚስጥራት መሆናቸው ይገለጻል። የጌታ ራት፣ እፅበተ እግር እና የኢየሱስ ክርስቶስ የጌተሰማኒ ጸሎት ከፀሎተ ሐሙስ መርሐ ግብር ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።













